የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ
የኢትዮጵያ ቮሊቮል ፌዴሬሽን ከዓለም አቀፍ ቮሊቮል ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በአራት ኪሎ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማእከል ከመስከረም 24-28/2003 ዓ.ም ሲሰጥ የቆየው ስልጠና መሰረታዊ የቮሊቮል አሰልጣኝነት ላይ ያተኮረ ነው ፡፡ በጽሁፍና በተግባር ሲሰጥ የቆየው በዚሁ ስልጠና 30 የሚሆኑ ከብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች፣ ከክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች የመጡ የታዳጊ ወጣቶች አሰልጣኞች እንዲሁም ተጫዋቾች የተውጣጡ ተሳታፊዎች ነበሩ ፡፡
Last Updated (Wednesday, 20 October 2010 18:26)
በሲንጋፖር የወጣቶች ኦሎምፒያድ ውጤት ላስመዘገቡ ስፖርተኞች ሽልማት ተሰጠ
አለም አቀፍ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የመጀመሪያውን የወጣቶች ኦሎምፒያድ በሲንጋፖር አካሂዷል፡፡ በዚህም 153 አባል ሀገሮች 3,525 ስፖርተኞቻቸውን አሳትፈዋል፡፡ ለሁለት ሳምንት ሲካሄድ በሰነበተው ውድድር ሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ የገቡት 27 ሀገሮች ብቻ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ በአትሌቲክስና በውሃ ዋና ያቀረበቻቸው ተተኪ ስፖርተኞች አኩሪ ውጤት በማስመዝገባቸው ከመንግሥትና ከኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ 200 ሺ ብር የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡
ነሐሴ 28/2002 ዓ.ም. ምሽት በሸራተን አዲስ ሆቴል ላሊበላ አዳራሽ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት በ1000 ሜትር በሁለቱም ፆታዎች የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙት መሀመድ አማን እና ትዝታ ቦጋለ እያንዳንዳቸው የ45ሺ ብር፣በ3000 ሜትር ተሳትፎ የብር ሜዳሊያ ላጠለቀው ፍቀሩ ፈይሳ እንዲሁም በ2000 ሜትር መሰናክል የብር ሜዳልያ ባለቤት ለሆኑት ፀሐይነሽ ፃሌና ሀብታሙ ጃለታ እያንዳንዳቸው የ25 ሺ ብር ሽልማት ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እጅ ተቀብለዋል፡፡
በውሃ ዋና በ50 ሜትር ጀርባ ቀዘፋ በራስዋ ተይዞ የነበረውን የኢትዮጵያ ሪከርድ ላሻሻለችው ያኔት ስዩም እና ሮቤል ኪሮስ ለየግላቸው 9 ሺ ብር ተሸልመዋል፡፡ በሽልማቱ የአትሌቲክስ አሰልጣኝ ሻምበል እሸቱ ቱራ የውሃ ዋና አሰልጣኝ አቶ ጌታቸው ውበቱ እንዲሁም ቡድን መሪው አቶ ኪሮስ ነጋ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
Last Updated (Wednesday, 15 September 2010 14:06)
የኢትዮጵያ ክብደት ማንሳትና የሰውነት መገንባት ፌዴሬሽን የታዳጊ ወጣቶች ኘሮጀክት ስልጠና ሊጀምር ነው
የኢትዮጵያ ክብደት ማንሳትና የሰውነት መገንባት ፌዴሬሽን ከ1968 ዓ.ም. ጀምሮ የስፖርት ክፍል ውስጥ ተጠቃሎ የነበረ ሲሆን በ1970 ዓ.ም. በፌዴሬሽን ደረጃ ተቋቁሟል፡፡ በፌዴሬሽን ደረጃ ከተቋቋመ ጀምሮ በሀገራችን ስፖርቱን ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ለማድረስ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን በመንደፍ ህዝባዊ አካሉን በማስተባበር አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ በአገር አቀፉና በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ በመሳተፉ አበረታች ውድድሮች ያደረገ ሲሆን እስከ አሁን ድረስ የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ኘሮጀክት የሌለው መሆኑ ይታወቃል፡፡
Last Updated (Wednesday, 15 September 2010 15:39)
የቀድሞ የዓላማችን የቼስ ስፖርት ተዋቂ የነበሩ ሀገራችን በመምጣት ሙያዊ ምክክር አደረጉ
የቼስ ስፖርት በዓለም አቀፍ በፌዴሬሽን ተቋቋመ ዘመናዊ እንቅሰቃሴ የጀመረው ከ1924 እ.ኤ.አ. ሲሆን በአገራችን ደግሞ በ1973 ዓ.ም. በፌዴሬሽን ደረጃ ተቋቁመው በ1986 ዓ.ም. የአለም አቀፍ የቼስ ፌዴሬሽን አባል ሆናለች፡፡ ስፖርቱ በሀገራችን ከተጀመረ ረጅም ዓመታት ቢያስቆጥርም በተፈለገው መጠን አድገት አሳይቷል ለማለት አያስደፍርም፡፡ ስለዚህ በአሁኑ ጊዜ ፌዴሬሽኑ ስፖርቱን ለማጠናከር ሰፊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ በለውጥ ሂደት ላይ መሆኑን ገለፀ
Last Updated (Monday, 13 September 2010 17:14) የኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን የሙያ ማሻሻያ ስልጠና ሰጠየኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን የካራቴ ስፖርትን ለማስፋፋትና ለማሳደግ ትኩረቱን በስልጠና ላይ በማድረግ ከነሐሴ 8 – 14/2002 ዓ.ም. በ4 ኪሎ ስፖርትና ትምህርት ማዕከል ጅምናዚየም የሙያ ማሻሻያ ፣የአንደኛ ደረጃ የአሰልጣኝነት ስልጠናና የዳን ፈተና በመስጠት በተሳካ ሁኔታ አጠናቅቋል፡፡ Last Updated (Wednesday, 01 September 2010 13:46) |
ለወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ
ከነሐሴ 6/12/02 – 9/12/02 ዓ.ም. በአሰላ ከተማ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እና ከጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ለተውጣጡ የሥራ አስፈፃሚዎችና ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና እና የልምድ ለውውጥ ኘሮግራም ተካሄደ፡፡ የኘሮግራሙ ዋና ዓላማ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ አጠናቆ ወደ ውጤት ተኮር ሚዛንና (BSC) እየገባ ስለሆነ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሥራ አስፈፃሚዎችና ሠራተኞች አቅም በመገንባት የተሻለ ሥራ እንዲሰሩ ለማድረግ ነው፡፡ የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ኘሮጀክት የብቃት መለኪያ ውድድር ተካሄደ
Last Updated (Wednesday, 01 September 2010 13:47) |
- ለአንድ ሣምንት በሐዋሳ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የዳርት ውድድር በኦሮሚያ ክልል የበላይነት ተጠናቀቀ
- የወጣት ማዕከላት የመፅሐፍት ልገሳ ኘሮግራም ተካሄደ
- በአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር የወጣቶች የዕድገት ፓኬጅ ዙሪያ ከአጋር አካላት ጋፐ ውይይት ተካሄደ
- የኢትዮጵያ ባድሜንተን ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ
- በፌዴራል መሥሪያ ቤቶች የስፖርትና መዝናኛ ኮማቴ ለማቋቋም ውይይት ተካሄደ
- የኢትዮጵያ ጅምናስቲክ ፌዴሬሽን የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ተጀመረ
- በአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር የወጣቶች የዕድገት ፓኬጅ ዙሪያ ከአጋር አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ
- የወጣቶች የፀረ.ኤች አይ. ቪ/ኤድስ ንቅናቄ ለማጠናከር የሚያስችል የአሠልጣኞች ስልጠና ተሰጠ
- በአፍሪካ ወጣቶችን የማልማትና የማብቃት ረቂቅ መርሀ-ግብር ላይ ውይይት ተካሄደ
- ህዝባዊ መሠረት ያለው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የተተኪ ስፖርተኞች ምንጭ ነው


የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ሀገር አቀፍ የሴቶች ውድድርን ከነሐሴ 25-29/2002 ዓ.ም. ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ በአራት ኪሎ ትምህርትና ስልጠና ማዕከል እንደሚያደርግ ነሐሴ 24/12/2002 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጠ ፡፡ የፌዴሬሽኑ ኘሬዚዳንት አቶ ተስፋዬ ሽፈራው በመግለጫው ላይ እንዳሳወቁት የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ስፖርቱን በሀገራችን ለማስፋፋትና ለማሳደግ በአሁኑ ጊዜ የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ (BPR) በማጥናት የሙከራ ትግበራ ላይ የሚገኝ ሲሆን በሙከራ ትግበራው ላይ ብዙ ሥራዎችን በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል ፡፡

የአገራችን ስፖርት የተወዳዳሪነት አቅም ለማሳደግና መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ከታቀዱትና ተግባራዊ እየሆኑ ካሉ ታላቅ አገራዊ ተግባራት መካከል የታዳጊ ወጣቶች የስልጠና ኘሮጀክት አንዱ ነው፡፡ ዕድሜአቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች በተመረጡ 155 ትምህርት ቤቶች በእግር ኳስ፣በመረብ ኳስና በአትሌቲክስ ስፖርቶች ከመስከረም 2000 ዓ.ም. ጀምሮ ለ3875 ታዳጊዎች ስልጠናው ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ስልጠናው በ109 ጣቢያዎች በእግር ኳስ፣በ40 ጣቢያዎች በመረብ ኳስ፣ በ6 ጣቢያዎች በአትሌቲክስ ስፖርት የወጣቶችና ስፖርት ሚ/ር፣የትምህርት ሚ/ር እና አገር አቀፍ ፌዴሬሽኖች በጋራ ሥራዎችን ሲያከናውኑ ቆይተዋል፡፡